ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን የመጠቀም ፍላጎቷን ያክል የውሃ ሀብቱን መጠበቅና ማስተዳደር ላይም ብዙ መስራት አለባት ተባለ
TRACK

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን የመጠቀም ፍላጎቷን ያክል የውሃ ሀብቱን መጠበቅና ማስተዳደር ላይም ብዙ መስራት አለባት ተባለ

Avatar

ግንቦት 28 2017

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን የመጠቀም ፍላጎቷን ያክል የውሃ ሀብቱን መጠበቅና ማስተዳደር ላይም ብዙ መስራት አለባት ተባለ።

በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶች በተለያየ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር ውስጥ እያለፉ መሆኑ ተነግሯል።

ረዘም ላሉ ዓመታት በስራ ላይ የቆየውን የኢትዮጵያ የውሃ ፖሊሲ ለማሻሻል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ረቂቅ ፖሊሲ አዘጋጅቷል።

በዚህ ፖሊሲ ውሃን በወጉ መንከባከብና ማስተዳደር በቂ የህግ ድጋፍ እንዲያገኝ ተደርጓል መባሉን ሰምተናል።

ረቂቅ ፖሊሲው ለውሃ ሃብት ጥበቃ እና ማስተዳደር ተገቢውን ትኩረት የሰጠ እንደሆነ በሚኒስቴሩ የውሃ ሃብት አስተዳደር የሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ በላይነህ ይርዳው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ውሃን ለመጠቀም የሰጠችውን ያህል ትኩረት ለማስተዳደሩ መንፈጓ የውሃ አካሎቿ በተለያዩ ችግሮች እንዲፈተኑ አድርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያን የውሃ አካሎች እየፈተኑ ናቸው ካሏችው ችግሮች መካከልም የአየር ንብረት ለውጥ፣በሰዎች አያያዝ ፤ በመጤ አረሞች እና በተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ምክንያት እየጠሙ ያሉትን ጠቅሰዋል።

አስራ ሁለት የውሃ ተፋሰሶች ያሏት ኢትዮጵያ ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱ ድንበር ተሻጋሪ ናቸው።

ዘጠኙ ደግሞ ከአንዱ የኢትዮጵያ ክልል ወደ ሌላ ክልል ይፈስሳሉ።

ቴዎድሮስ ወርቁ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar