ጥቅምት 25 2018
በኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ ሐውልት እንዳያቆም እና የቆሙትን ማንም ባሻው ሰዓት እንዳያፈርስ የሚከለክል የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተጠየቀ፡፡
ይህ ጥያቄ የቀረበው ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት (ወመዘክር) ”ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን “በሚል ርዕስ በተሰናዳ ሥነ ጥባባዊ ወይይት ላይ ነው፡፡
የውይይቱን መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአለ ሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዲን ሠዓሊ አገኝሁ አዳነ የዘመን መልክ የሆኑ በሶስት ተከታታይ መንግስታት የተሰሩ የአደባባይ ሐውልቶችን የተመለከተ ዳሰሳ አቅርበዋል፡፡
ዳሰሳው የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ማዕከል የሆነቸውን አዲስ አበባን መሰረት ተደርገው የተሰሩትን ሐውልቶች የተመለከተ ነው፡፡
Comments