የሪል ስቴት ዘርፍ የሚመራ እና የሚተዳደርበት ህግ ባለመኖሩ ቤት ገዢዎች ካርታ ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑንን ተነገረ
TRACK

የሪል ስቴት ዘርፍ የሚመራ እና የሚተዳደርበት ህግ ባለመኖሩ ቤት ገዢዎች ካርታ ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑንን ተነገረ

Avatar

መጋቢት 26፣2016

ቢሊዮን ብር የሚገላበጥበት የሪል ስቴት ዘርፍ የሚመራ እና የሚተዳደርበት ህግ ባለመኖሩ በተለይ ቤት ገዢዎች ካርታ ለማግኘት እየተቸገሩ መሆኑንን ተነገረ፡፡

መንግስት በበኩሉ ችግሩን አውቀዋለሁ ለመፍትሄውም እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

እነዚህ ቤት ገንቢዎች ከመንግስት መሬቱን ከተረከቡ በኋላ በራሳቸው ስም በማድረግ ካርታውን በመያዝ ከባንክ ብር እየተበደሩ እንደሚጠቀሙ እና ለባለቤቱ ካርታውን በጊዜ እንደማያስረክቡ ተነግሯል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ሁሉንም ቤት ገንቢዎች አያካትትም ተብሏል፡፡

የዛሬ ሶስትና አራት አመት 60 እና 70 ሺህ ብር የነበረው ካርታን ወደ ራስ ማዞሪያ በዚሁ በሪል እስቴት ገንቢዎች ማንዛዛት ምክንያት፤ አሁን ላይ ቤት ገዢዎች መንግስት ከሰባት መቶ ሺህ ብር በላይ እየጠየቀን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ሪል_ስቴት #የቤት_ካርታ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comments

Avatar