ለ 5 አመታት ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ነገ በወላይታ ሶዶ እንደሚካሄድ ተነገረ
TRACK

ለ 5 አመታት ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ነገ በወላይታ ሶዶ እንደሚካሄድ ተነገረ

00:00

የካቲት 8፣2016

ለአምስት አመታት ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም በነገው ዕለት በወላይታ ሶዶ እንደሚካሄድ ተነገረ።

በሁነቱ ላይ ለመሳተፍ እስከ አሁን ከ125 የሚበልጡ የከተሞች ተወካዮች ወላይታ ሶዶ ገብተዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም መጀመሪያ ላይ ሲከበር የቆየው የከተሞች ቀን በሚል ነበር።

በዚሁ ስያሜ ለአምስት ዙር መከበሩን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ኢትዮጵያ በደቻ አስታውሰዋል፡፡

ስድስተኛው ዙር ላይ ስያሜው ወደ ኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም መቀየሩን ተናገረዋል፡፡

ሶስት ዙሮች በዚው ስያሜ ተከብሮ መሃል ላይ መቋረጡን ጠቅሰዋል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የነበሩ ግጭቶች እና በአለም ደረጃ የተከሰተው የኮረና ወረርሽኝ አከባበሩ መሃል ላይ እንዲቋረጥ ያደረጉ ምክንያቶች ነበሩ ብለዋል፡፡

ነገ በይፋ ተከፍቶ እስከ ፊታችን አርብ ይቆያል በተባለው በዚህ ፎረም ላይ የፓናል ውይይቶች እንደሚኖሩ ተጠቅሷል።

ከተሞች ያሏቸውን የኢቨስትመንት አማራጮች የሚያስተዋውቁባቸው መድረኮችም እንደሚዘጋጁ አቶ ኢትዮጵያ ከወላይታ ሶዶ በስልክ ነግረውናል።

ንጋቱ ረጋሳ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የከተሞች_ፎረም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00