የኃይል መቆራረጥን ይቀርፋሉ የተባለላቸው ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል
TRACK

የኃይል መቆራረጥን ይቀርፋሉ የተባለላቸው ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል

00:00

የካቲት 8፣2016

የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን ይቀርፋሉ የተባለላቸው ከ 146 በላይ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል።

የመስመር ዝርጋታ፣ ፖሎችን የመቀየር፣ የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም ተነግሯል ።

በነዋሪዎችና በተለያዩ ተቋማት ለሚነሱ የመብራት መቆራረጥ ችግሮች እልባት ይሰጣሉ የተባሉ ስራዎች እስካሁን ሲከወኑ መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ገብሬ ተናግረዋል።

አቶ ዮሐንስ አክለውም በመዲናዋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ብዙ ስራዎችን እየሰራን ቢሆንም አሁንም በመሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጠሩ አደጋዎች፣ ስርቆቶች፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የመስመር ፖሎች መኖር እና መሰል ችግሮች የሃይል መቋረጥ ችግር እንዲያጋጥም ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

የመብራት መቆራረጥ ችግር አሁንም ፈተና ሆኖ መቀጠሉንና ችግሩም ከግለሰብ አልፎ የተቋማትም ችግር እንደሆነ ዘልቋል ተብለሏል።

ፍቅሩ አምባቸው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የመብራት_መቆራረጥ #የኤሌክትሪክ_ኃይል

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00