መጠለያው ትምህርት ቤት መሆኑን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች የቀሩት በመሆኑ ስጋት ውስጥ ገብተናል ይላሉ
TRACK

መጠለያው ትምህርት ቤት መሆኑን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች የቀሩት በመሆኑ ስጋት ውስጥ ገብተናል ይላሉ

Avatar

ነሐሴ 29፣2016

በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ የመሬት መንሸራተት አደጋ በማጋጠሙ ምክንያት ቀያቸውን ለቀው በመጠለያ ውስጥ ላሉ ከ300 በላይ ነዋሪዎች የሚደረገው የምግብ አቅርቦት ቀንሷል ተባለ፡፡

ከዚህ ቀደም ተፈናቃዮቹ ሲረዱ የነበረው ከከተማዋ ነዋሪዎች በሚገኝ እና በከተማዋ ከሚገኙ ተቋማት እንደነበር ተነግሯል፡፡

ይህንን የተናገረው የደሴ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ነው፡፡

ከአደጋው ሸሽተው በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ያሉት ነዋሪዎችም የሚሉትም ይህንኑ ነው፡፡

መጠለያ ጣቢያው ትምህርት ቤት መሆኑን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች የቀሩት በመሆኑ ስጋት ውስጥ ገብተናል ይላሉ፡፡

Comments

Avatar