አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን በሚከውነው ስራ ለመጭዎቹ 5 ዓመታት 60 ቢሊየን ብር ያስፈልገኛል አለ
TRACK

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን በሚከውነው ስራ ለመጭዎቹ 5 ዓመታት 60 ቢሊየን ብር ያስፈልገኛል አለ

00:00

ግንቦት 27፣2016

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን በሚከውነው ስራ ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት 60 ቢሊየን ብር ያስፈልገኛል አለ፡፡

ከመንግስት 25 ቢሊየኑን ለማግኘት እቅድ መያዙን ተናግሯል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ይታወቃል፡፡

በተለይም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት መንገዱን ከጀመረ 8 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን እየሄደበት ያለው መንገድ ጥሩ ጅምር ነው ተብሏል፡፡

በተለይም የሽግግር ሂደቱ 2 ዓመት እንደሚፈጅ የሚነገረው የራስ ገዝነት ሂደቱ በቀሪ ጊዜያት፤ ሂደቶች ተጠናቀው ዩኒቨርሲቲው በይፋ እራስ ገዝ መሆን እንደሚችል እርግጠኛ መሆኑን በጉዳዩ ላይ የዩንቨርስቲው ኃላፊዎች ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

Comments

00:00