በአዲስ አበባ ካሉ ከ20,000 በላይ ህንፃዎች የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ያሟሉት 42ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡
TRACK

በአዲስ አበባ ካሉ ከ20,000 በላይ ህንፃዎች የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ያሟሉት 42ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

00:00

ታህሳስ 22፣2017

በአዲስ አበባ ካሉ ከ20,000 በላይ ህንፃዎች የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ያሟሉት 42ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

ይህንን ያለው የከተማዋ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው፡፡

ኮሚሽኑ መስርቶቹን የማያሟሉ የተቋማትና የግለሰብ ህንፃዎች ላይ በቅርቡ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ ብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ይከፈለው ወልደመስቀል እንደነገሩን፤ ከ4ፎቅ በላይ የሆነ የትኛውም ህንፃ የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት የሚደነግግ ደምብ ወጥቷል፡፡

ለመሆኑ የአደጋ መከላከል መስፈርቶቹ ምን ምን ናቸው?

አንድ ህንፃ ጅምር የእሳት ማጥፊያ፣ አውቶማቲክ የእሳት አደጋ መከላከያ ማስገጠም፣ የአደጋ መከላከል ምልክቶችን በሚታይ ቦታ ማስቀመጥ፣ አመቺ የአደጋ ጊዜ መውጫ የግድ ሊኖረው ይገባል ተብሏል፡፡

በተለይ እንደ ሆቴል ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሆኑ የሰለጠኑ የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ሊኖራቸው እንደሚገባ ተደንግጓል፤ባለሙያዎቹን እኛ እናሰለጥንላቸዋለን ብለውናል፡፡

Comments

00:00