ግንቦት 12/2018
በምርጫ ወቅት "በታንዛኒያ እና በዩጋንዳ "ላይ የተስተዋለው የኢንተርኔት ገደብ ወይም እቀባ በኢትዮጵያ እንዳይኖር የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውን ተናገሩ።
የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን ለመታዘብ በቂ ዝግጅት ማድረጉን እና የምርጮ ቦርድ ውሳኔን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል።
ይህ የተነገረው ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ፓራዳይም ኢንሼቲቭ ከተሰኘ መንግስታዊ ካለሆነ ተቋም ጋር በመሆን በዲጂታል መብት ላይ ባሰናዳው ወይይት ላይ ነው።
በራዲሰን ብሉ (Radison blue) ሆቴል በተካሄደው ውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ፣የኢትዮጵያ መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣የኢትዮ ቴሌኮም ፣የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና የሌሎች ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
Comments