ደንብ ተላላፊዎች ላይ የተጣለው ቅጣት ከፍ ማለቱ በከተማዋ በሚታየው ሥርዓት ይዞ አለማሽከርከር ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?
TRACK

ደንብ ተላላፊዎች ላይ የተጣለው ቅጣት ከፍ ማለቱ በከተማዋ በሚታየው ሥርዓት ይዞ አለማሽከርከር ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?

Avatar

ሚያዝያ 15 2017

በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ በተደረገው የትራፊክ ደንብ ጥሰት ቅጣት የተነሳ አሽከርካሪዎች ሲማረሩ ይሰማል፡፡

የቅጣት መጠኑ ከፍ ማለቱ አጥፊ አሽከርካሪዎችን እንዲሰማቸው እያደረገ ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡

ለመሆኑ የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የተጣለው ቅጣት ከፍ ማለቱ በከተማዋ በሚታየው ሥርዓት ይዞ አለማሽከርከር ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤሊያስ ዘርጋ ነባሩ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ የገንዘብ ቅጣቱ አነስተኛ በመሆኑ ደንብ የሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ በትራፊክ አደጋም የሚጎዳው የህብረተሰብ ቁጥር እያሻቀበ በመሆኑ በአዲሱ ደንብ የቅጣት መጠኑን ከፍ ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል፡፡

ነዳጅ በመወደዱ ቅጣቱ ይቀንስልን የሚል አስተያየትና መከራከሪያ ነጥብ ተቀባይነት አይኖረውም ሲሉም ይናገራሉ፡፡

በአዲሱ ደንብ የገንዘብ ቅጣቱ ከፍ እንዲል መደረጉም የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን እንዲቀንሱ አስችሏል ሲሉም ኢንጂነር ኤልያስ ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪዎች በየጊዜው ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች መካከል ደግሞ ባላጠፋነው ደንብ እየተቀጣን ነው፤ ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤትም አቤቱታ ብናቀርብም ፍትህ እያገኘን አይደለም የሚል ነው፡፡

Comments

Avatar