በኢትዮጵያ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዚህ በፊት በማይታወቁ የወባ በሽታ አምጭ ትንኞች የሚከሰት የወባ በሽታ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
TRACK

በኢትዮጵያ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዚህ በፊት በማይታወቁ የወባ በሽታ አምጭ ትንኞች የሚከሰት የወባ በሽታ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ

Avatar

ሐምሌ 4፣ 2016

በኢትዮጵያ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዚህ በፊት በማይታወቁ የወባ በሽታ አምጭ ትንኞች የሚከሰት የወባ በሽታ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ፡፡

የወባ በሽታ ስርጭቱ ቀንሶ የነበረ ቢሆንም፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ግን በወረርሽኝ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በሀገሪቱ ስርጭቱ እየሰፋ ያለውን የወባ በሽታ ለመከላል የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበሮችን እና የመመርመሪያ ኪቶችን በማቅረብ ዩኤስኤአይዲ(USAID)ኢትዮጵያ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የወባ በሽታ መከላከሉ ላይ ካጋጠሙ ችግሮች ውስጥም ከዚህ ቀደም ያልነበሩ እና መድሃኒት የተላመዱ አዲስ ዝርያ የሆኑ የወባ አምጭ ትንኞች መከሰታቸውን የሚናገሩት በዩኤስኤአይዲ ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ም/ዳይሬክተር የሆኑት ህሊና ወርቁ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

Comments

Avatar