የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ በሃገር ውስጥ ያሉ ባንኮች ከውድድር ሜዳው ይወጣሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የም/ቤት አባላት ተናገሩ
TRACK

የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ በሃገር ውስጥ ያሉ ባንኮች ከውድድር ሜዳው ይወጣሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የም/ቤት አባላት ተናገሩ

Avatar

ሰኔ 19፣ 2016

የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ በሃገር ውስጥ ያሉ ባንኮች ከውድድር ሜዳው ይወጣሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡

የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበለትን የውጭ ባንኮች በሀገሪቱ እንዲሠማሩ የሚፈቅደው የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህም ወቅት የውጭ ሃገር ባንኮች የሃገር ውስጥ የባንክ ገበያን እንዲቀላቀሉ ሲፈቀድ የዘመነ የባንክ አሰራርና የውጭ ምንዛሪን ያመጣሉ በሚል ታምኖባቸው ቢሆንም የሀገር ውስጥ ባንኮች የመወዳደር አቅም ላይ ጥያቄ አለን፣ እንዳያከስሟቸውም እንሰጋለን ብለዋል የምክር ቤት አባላቱ፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በተጨማሪም የገበያ ውድድሩን ሚዛን ለመጠበቅ ወደ ስራ የሚገቡትን የውጭ ሃገራት ባንኮችን ለመቆጣጠር አሰራር መዘርጋት አለበት፤ የሀገር ውስጥ ባንኮችም አቅማቸውን እንዲያሻሽሉ መታገዝ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

Comments

Avatar