የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክረምቱ ዝናብ በሚያስከትለው ጎርፍ  የሚፈናቀሉ ሰዎች ካሉ በሚል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉን ተናገረ
TRACK

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክረምቱ ዝናብ በሚያስከትለው ጎርፍ የሚፈናቀሉ ሰዎች ካሉ በሚል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉን ተናገረ

Avatar

ሰኔ 6፣ 2016

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የክረምቱ ዝናብ በሚያስከትለው ጎርፍ የሚፈናቀሉ ሰዎች ካሉ በሚል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉን ተናገረ።

ኮሚሽኑ እንዳለው ጎርፍ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ ቦታዎች መጋዘኖች ተዘጋጅተው የዕለት ደራሽ ምግብ ተቀምጦባቸዋል።

በውሃ የተከበቡ ያሉ ሰዎችን ለማውጣት የሚረዱ ጀልባዎችንም አዘጋጅቻለሁ ብሏል።

የክረምቱን መግባት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፤ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፤ መረጃ እና ኦፕሬሽን መሪ ስራ አስፈጻሚ ተወካይ ዶክተር ፍራኦል በቀለ ነግረውናል።

የመጀመሪያው የዝግጅት ስራ ለሰዎች መረጃ መስጠት ነው ብለዋል።

መረጃ ከመስጠት በሻገር መፈናቀል ቢያጋጥም በሚል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ነው ሲሉም ዶክተር ፍራኦል ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች በተዘጋጁ መጋዘኖች የዕለት ደራሽ ምግብ እየያዝንባቸው ነው ሲሉ ተወካዩ ነግረውናል።

በዘንድሮው ክረምት በአጠቃላይ ምን ያህል ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ተፅዕኖ ሊያገኛቸው ይችላል? በሚል የጠየቅናቸው ዶክተር ፍራኦል ተከታዩን መልሰዋል።

በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው በተባሉ አካባቢዎች ያሉ ሰዎች የዝናቡን ሁኔታ በተመለከተ የሚሰጡ መረጃዎችን እንዲከታተሉ ተመክረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…

ንጋቱ ረጋሣ

Comments

Avatar