ሚያዝያ 14 2017
በጎረቤት ሱዳን ያለውን ጦርነት በመስጋት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከገቡ ስደተኞች ከ40,000 የሚበልጡትን ወደ አንድ የመጠለያ ጣቢያ የማምጣት ስራ መከናወኑ ተነገረ።
በጎረቤት ሡዳን ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት በመስጋት በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች እና በዚያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሁንም እየገቡ ናቸው ተብሏል።
ወደ ክልሉ የገቡት ተፈናቃዮች በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እና በየሰው ቤት ማረፋቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።
በየሰዉ ቤት የተጠለሉት ተፈናቃዮች በሡዳን የነበሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው ያሉን ኮሚሽነር አብዱልአዚዝ ፤ሡዳናውያን ዜጎች ግን በየአካባቢው በተዘጋጁ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ማረፋቸውን ነግረውናል።
Comments