ህዳር 13፣2017
በሀገሪቱ ሰራተኞች ላይ የስራ ባህላቸው ዝቅተኛ ነው፤ እየተባለ ለሚቀርበው ክስ ችግሩ የሰራተኛው ብቻ ሳይሆን የአሰሪውም ጭምር ነው ሲል የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌደሬሽን ተናገረ፡፡
የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌደሬሽን በተደጋጋሚ በሀገሪቱ ያለው የስራ ባህል ዝቅተኛ ነው እየተባለ በሰራተኛው ላይ የሚቀርበው ክስ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግሯል፡፡
የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወርቁ ታምራት በሰራተኛው ላይ ብቻ ሚቀርበው ክስ ልክ እንዳልሆነ ተናግረው ‘’አሰሪዎችም ሆኑ ሰራተኞች የስራ ባህላችን ተመሳሳይ ነው’’ ብለዋል፡፡
ሰራተኛው ብቁ እንዲሆን ከተፈለገ ደግሞ ቤተሰብም፣ መንግስትም፣ አሰሪውም በአግባቡ የቤት ስራቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አሳስበዋል፡፡
Comments