ጥቅምት 19፣2016
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በህገወጥ መንገድ ከሀገር ወጥተው ባስቸጋሪ ሁኔታ የቆዩ ከ135,000 በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልስዋል፡፡
በሌላ በኩል በዚሁ ዓመት በህጋዊ መንገድ 100,000 ዜጎች ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ በመንግስት ተልከዋል፡፡
ይህም ህገ-ወጥ ስደቱ ምን ያህል በቁጥር የላቀ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ለስደቱ ገፊ ከሆኑ የተለያዩ ምክንያቶች ባሻገር ማህበራዊ ተቋማት እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች አበረታች መሆናቸው ችግሩን አባብሶታል ተብሏል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
#Ethiopia #ShegerWerewoch #ህገወጥ_ስደት #አረብ_ሀገራት #ሳውድ_አረቢያ #የመን_ሰንዓ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments