00:00
ሐምሌ 3፣ 2016
መንግስት በየቦታው የሚፈፀሙ እገታዎችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡
እተፈፀሙ ያሉ እገታዎች የሰዎችን የመንቀሳቀስ መብት እየገደቡ መሆኑንና በሰላም ወጥቶ መግባት ቅንጦት እየሆነ መምጣቱን የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት የቅድሚያ ቅድሚ ሃላፊነቱና መንግስት የሚያሰኘው ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆን ሲገባው ይህ እየሆነ አለመሆኑ ያሳስበናል ያሉት አቶ ደስታ፤ አሽከርካሪዎች፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የሚሰሩ ሰዎች እንዲሁም ተማሪዎች በሚፈፀምባቸው እገታ ወጥተው እየቀሩ ነው፣ስለዚህም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ በየስፍራው የሚፈፀሙ እገታዎችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል፡፡
ማስቆም ካልቻለም አለመቻሉን ለህዝቡ ያሳውቅ ብለዋል ሰብሳቢው፡፡
Comments
00:00