TRACK
የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ።
ሚያዝያ 14/2018
በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የቋረጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ስራ ለማስጀመር ከየአካባቢው አስተዳድሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ።
ግጭቶች ባሉባቸው በሁሉም አካባቢዎች 14 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተቋርጠው መቆየታቸውን የነገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ አብዱረህማን የፀጥታው ሁኔታ መሻሻል የታየባቸው አካባቢዎች ያሉ ፕሮጀክቶችን ዳግም ስራ መጀመሩን ነግረውናል።
Comments