TRACK
‘’ቀን ከለሊት ዋጋ የሚከፍሉ የፀጥታ አካላት እንዳሉ ሁሉ፤ በህግ ላይ የሚያምጹ የፀጥታ አካላትም አሉ’’ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ
ሚያዝያ 29 2017
የፌዴራል መንግስት የማያውቃቸው በክልሎች የሚተዳደሩ 297 ኬላዎች መኖራቸው ተነገረ፡፡
ኬላዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር እንዲነሱ የተወሰኑ፤ ነገር ግን እስከአሁን ያልተነሱ በክልሎች የሚተዳደሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ይህ የተነገረው የገቢዎች ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የ9 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
በምክር ቤቱ የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሎች እንዲነሱ የተወሰኑ ኬላዎች ባለመነሳታቸው በገቢ እና ወጪ ንግዶች ላይ እንዲሁም በሸቀጦች ነፃ ዝውውር ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ እንደሆነ ማረጋገጡን ተናግሮ ለምን ኬላዎች እንዳልተነሱ ጠይቋል፡፡
የጉሙሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ‘’ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በተገኙበት በተደጋጋሚ አቅጣጫ ቢስጡበትም ችግሩ ቀጥሏል’’ ብሏል፡፡
በፓርቲ ጉባኤዎች ላይ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭምር በክልሎች ያሉ የፌደራል መንግስት የማያውቃቸው ኬላዎች እንዲነሱ መመርያ ቢተላለፍም በቅርቡ የፀጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ላይ በተደረገ ጥናት 297 ኬላዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል፡፡
Comments