የህብረቱ ጉዞ ወዴት ይሆን?
TRACK

የህብረቱ ጉዞ ወዴት ይሆን?

Avatar

የካቲት 8 2017

የአፍሪካ ሀገራት ለብዙ ዓመታት በአውሮፓ እና በአሜሪካ የልማትና የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ስር ኖረዋል፡፡

ምድራቸው ሳያጣ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት እና በመሪዎቻቸው ሀብት፣ ንብረት ዘረፋ ምክንያት ህዝቦቹ ከተመፅዋችነት አልፈው ክብር እንዲያጡ ከሆነ ረዥም አመታት ተቆጥረዋል፡፡

በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት ለውጪ ሀገራት ይሰጥ የነበረውን የልማት እና የሰብአዊ አገልግሎት ድጋፉን ለ90 ቀናት በማቋረጡ በአፍሪካ መንግስታት ዘንድ ቀን የጨለመ ያህል ተቆጥሯል፡፡

ለመሆኑ በሚሊዮኖች አንዳንዴም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦችን የሚመሩ መንግስት የሀገራቸውን ሀብት አሰባስቦ ከመጠቀም ይልቅ በእርዳታ ላይ ጥገኛ ሆነን እንቀጥል ማለታቸው አያሳስብም ወይ? የህብረቱ ጉዞ ወዴት ይሆን?

የኔነህ ሲሳይ

Comments

Avatar