መንግስትም በአስር ዓመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን 500,000 ለማድረስ ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ይናገራል
TRACK

መንግስትም በአስር ዓመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን 500,000 ለማድረስ ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ይናገራል

Avatar

ግንቦት 13 2017

በኢትየጰያ የኤሌክትሪክ መኪኖች በየጎዳናው ላይ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

መንግስትም በአስር ዓመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን 500,000 ለማድረስ ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ይናገራል፡፡

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በዘርፉ ለሚሰማሩ ተቋማት የተለያዩ የፖሊሲ ማበረታቻዎች እየተሰጠ መሆኑን ተከትሎ አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሰሩ መንገድ ከፍቷል ተብሏል፡፡

ከነዚህም መካከል ከቀናት በፊት የቻይናው ጂኤሲ #GAC ግሩፕ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሸጫ የንግድ ማዕከል ከፍቷል፡፡

በሂደትም ተሸከርካሪዎቹን በኢትዮጵያ የማምረት ውጥን እንዳለው የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመኪና ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ተናግሯል፡፡

Comments

Avatar