ጥር 1/2018
በአዲስ አበባ አንዳንድ የወረዳ አመራሮች ተገልጋዩን ያመነጫጭቃሉ፣ ለጥያቄም ምላሽ አይሰጡም የሚል ቅሬታ ቀረበባቸው።
የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ በአግባባቡ ስራቸውን መስራት ያልቻሉ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አንደሆነ አስረድቷል፡፡
ቅሬታው የቀረበባቸው የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በስድስት ወራት የስራ ክንውን ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከሚመለከታቸው የከተማው ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።
የወይይቱ ተሳታፊዎች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳ ሲያቀኑ በሁሉም ባይሆንም በአንዳንድ አመራሮች ማመነጫጨቅ እና ማንገላታት እንደሚያጋጥማቸው እንዲሁም ለጥያቄያቸው ምላሽ እንደሚነፍጓቸው ተናግረዋል።
Comments