ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚቀርቡ የተለያዩ መድሃኒቶች በህገወጥ መንገድ ወጥተው በግል የመድኃኒት መሸጫዎች የሚሸጡባቸው አጋጣሚዎች አሉ
TRACK

ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚቀርቡ የተለያዩ መድሃኒቶች በህገወጥ መንገድ ወጥተው በግል የመድኃኒት መሸጫዎች የሚሸጡባቸው አጋጣሚዎች አሉ

Avatar

ህዳር 30፣2017

ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚቀርቡ የተለያዩ መድሃኒቶች በህገወጥ መንገድ ወጥተው በግል የመድኃኒት መሸጫዎች የሚሸጡባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

በዚህም ላይ ቅሬታ የሚያቀርቡ ብዙዎች ናቸው፡፡

በመንግስት የህክምና ተቋም ላይ በ200 እና በ300 ብር የሚገኙ እንደ ኢንሱሊን ያሉ መድሃኒቶች በድብቅ ወጥተው በግል የመድኃኒት መደብሮች እስከ 1,200 ብር ድረስ ዋጋ እየተቆረጠላቸው እንደሚሸጡ ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ።

ይህ የሚሆነው ሆን ተብሎ በሚፈጠር ሰው ሰራሽ ምክንያት እንጂ የመድኃኒቶች እጥረት በመኖሩ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ይናገራል።

ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚቀርቡ መድሃኒቶች በግል ተቋማትም እንዲገኙና እንደዚህ አይነት ችግር ዳግም እንዳይፈጠር ለግል የጤና ተቋማትና ማቅረብ እንደጀመረ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የግዥ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ለሸገር ሬዲዮ ነግረዋል።

Comments

Avatar