በአዲስ አበባ ህገ ወጥ ናችሁ በተባሉ 50,000  ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
TRACK

በአዲስ አበባ ህገ ወጥ ናችሁ በተባሉ 50,000 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

00:00

ሐምሌ 2፣ 2016

በአዲስ አበባ ህገ ወጥ ናችሁ በተባሉ 50,000 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

በከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ያሉ ከ400,000 በላይ ነጋዴዎች መኖራቸውን የሚናገረው የከተማዋ ንግድ ቢሮ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ነጋዴዎች ህገ ወጥ ሆነው ተገኝተዋል ብሏል፡፡

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሰውነት አየለ በዓመቱ ባደረግነው የቁጥጥር ስራ 50,100 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ገሚሱ ላይ የማሸግ እርምጃ ሲወሰድባቸው ሌሎቹ ደግሞ የንግድ ፈቃዳቸው ታግዷል፣ የተቀሩት በማስጠንቀቂያ ታልፈዋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የነዋሪውን የኑሮ ጫና ያቃልላሉ ተብለው በከተማዋ ባሉ መግቢያና መውጫ በሮች በተከፈቱት የገበያ ማዕከላት የግብርና ምርቶች ከገበያው ዋጋ ከ15-20 በመቶ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ምርቶችን እየሸጡ መሆኑን ጤፍን ለአብነት በመጥቀስ ነግረውናል፡፡

በገበያው ላይ ከ16,000 17,000 ብር እየተሸጠ ያለው ጤፍ በእነዚህ ገበያዎች ግን ከ12,000 ብር ጀምሮ እየተሸጠ መሆኑን ያነሳሉ፡፡

Comments

00:00