ሰኔ 12 2017
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ለመተግበር የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ኢትዮጵያ መጨረሷ ተነገረ።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳለው ስምምነቱን ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል የታሪፍ ማሻሻያ ሰነድ የፀደቀ ሲሆን በቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል።
ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ስራ ላይ ለማዋል ይረዳል የተባለ የፕሮጀክት ድጋፍም ከአውሮፓ ህብረት መገኘቱ ተሰምቷል።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር በ2018 በሩዋንዳ ኪጋሊ በ44 የአህጉሩ ሀገራት መፈረሙ ይታወሳል።
Comments