በግሉ የህክምና ዘርፍ የሚቋቋሙ ማዕከላት ኢትዮጵያን ለህክምና የምታጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ተባለ
TRACK

በግሉ የህክምና ዘርፍ የሚቋቋሙ ማዕከላት ኢትዮጵያን ለህክምና የምታጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ተባለ

Avatar

ጥር 2፣2017

በግሉ የህክምና ዘርፍ የሚቋቋሙ አዳዲስ ማዕከላት የተገልጋዮችን መብቶች ያከበሩ ኢትዮጵያንም በውጭ ሀገር ህክምና የምታጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ተባለ፡፡

በማህፀንና ጽንስ እንዲሁም በህፃናት ህክምና ላይ በተሰማሩ ባለሞያዎች የተቋቋመው ‘’ታይም የእናቶች ህፃናት ጤና እና የቀዶ ህክምና ማዕከል’’ ወደ ስራ መግባቱ ተነግሯል፡፡

በባለሞያዎቹ በጋራ የተመሠረተው የህክምና ማዕከል በኢትዮጵያ ጥቂት ባለሞያዎች ያሉትንና ለላቀ ህክምና የውጭ ሀገር ጉዞ የሚጠይቁ አገልግሎቶችን እዚሁ ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በተለይ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በተሻለ መልኩ ለማገልገል በዘርፉ ባለሞያዎች ማዕከሉ መመስረቱን የሚናገሩት ከማዕከሉ መስራቾች አንዱና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር አታክልቲ ጸጋይ ናቸው፡፡

የእናቶችና የህፃናት ጤና እጅግ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮችና የአንድ ሀገር የጤና ተቋም እንደመስፈርት ከሚወሰድባቸው አገልግሎቶች ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡

የህክምና ማዕከሉ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑንም ዶክተር አታክልት የተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar