ግንቦት 27 2017
ባለባቸው የምግብ እጥረት የተነሳ ህፃናት ለሞት ተጋላጭ የሆኑባቸው የህፃናት ማሳደጊያ መኖራቸውን በክትትሌ ደርሼበታለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንኑ በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች መፈፀም አለመፈፀማቸውን መገምገሙን አስረድቷል፡፡
በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት መካከል በአንዳንዶቹ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቀጠሉባቸው ተቋማት መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናግሯል፡፡
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ አዳማ ሐረር ሀዋሳ ሻሸመኔና ወላይታ ከተሞች በሚገኘው 21 የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ አኳያ ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው ምክር ሃሳቦች ምን ያህሉ ተፈጽሟል የሚለውን እና ግኝቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡
Comments