በተለያዩ ወንጀሎች ለተከሰሱ እና የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች መንግስት በነፃ ተከላካይ ጠበቃ እንደሚያቆም አሁንም ብዙ ሰዎች አያውቁም ተባለ
TRACK

በተለያዩ ወንጀሎች ለተከሰሱ እና የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች መንግስት በነፃ ተከላካይ ጠበቃ እንደሚያቆም አሁንም ብዙ ሰዎች አያውቁም ተባለ

Avatar

ሐምሌ 10፣ 2016

በተለያዩ ወንጀሎች ለተከሰሱ እና የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች መንግስት በነፃ ተከላካይ ጠበቃ እንደሚያቆም አሁንም ብዙ ሰዎች አያውቁም ተባለ።

መንግስት ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጡ ዘጠና ተከላካይ ጠበቆችን እንደመደበ ሠምተናል።

ይህን አገልገሎት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር በተቋቋመው የተከላካይ ጠበቆች ፅህፈት ቤት አማካይነት እየሰጠ ይገኛል።

አገልግሎቱ የሚሰጠው ተከሳሾቹ በገንዘብ ችግር ምክንያት ያለ ጠበቃ ክርክር ቢያካሂዱ የፍትህ መጓደል ሊገጥም ይችላል ብሎ፤ ፍርድ ቤት ላመነባቸው ሰዎች ነው ሲሉ የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አቶ ደሳለኝ ከበደ ነግረውናል።

ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው 2106 በጀት ዓመትም በ13874 መዝገቦች በወንጀል ለተከሰሱ፤ ከ35,000 በላይ የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ሰዎች መንግስት በነፃ ተከላካይ ጠበቃ ማቆሙን ከአቶ ደሳለኝ ሠምተናል።

Comments

Avatar