የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ማህበር በመንግስት በሚከወኑ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ እየተደረጉ አይደለም አለ
TRACK

የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ማህበር በመንግስት በሚከወኑ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ እየተደረጉ አይደለም አለ

00:00

ሐምሌ 3፣ 2016

የኢትዮጵያ ስራ ተቋራጮች ማህበር በመንግስት በሚከወኑ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ እየተደረጉ አይደለም አለ፡፡

በዚህም ምክንያት ‘’የሃገር ውስጥ ተቋራጮች ስራ አጥተዋል’’ ያለ ሲሆን ‘’በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚከወኑ ፕሮጀክቶችም ተሳትፎቸው አነስተኛ ነው’’ ብሏል፡፡

‘’የሀገር ውስጥ ተቋራጮችን መብት ለማስከበር የሚያግዝ ህግ ቢኖርም ህጉ እና መመሪያው እየተተገበረ አይደለም’’ ብሏል ማህበሩ።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግርማ ሀብተማርያም ‘’ከአዲስ አበባ ባለፈ በሀገር ውስጥ የሚከወኑ የልማት ስራዎች የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በበቂ ሁኔታ እንዲሳተፉ በህግ ቢቀመጠም ለሀገር ውስጥ ተቋራጮች የሚሰጠው አመለካከት የተዛባ በመሆኑ ህጉ የሚፈቅደልንን መብት እየተከበረልን አይደለም’’ ብለዋል።

Comments

00:00