በግብርና ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ባለሀብቶች በጦርነት እና በሌሎች ምክንያት ከዘርፉ ወጥተው ነበር ተባለ፡፡
TRACK

በግብርና ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ባለሀብቶች በጦርነት እና በሌሎች ምክንያት ከዘርፉ ወጥተው ነበር ተባለ፡፡

00:00

ሐምሌ 15፣ 2016

በግብርና ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ባለሀብቶች በጦርነት እና በሌሎች ምክንያት ከዘርፉ ወጥተው ነበር ተባለ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 6 የሚሆኑት በአማራ ክልል የነበሩ ናቸው፡፡

ከ10ሩ ባለሀብቶች የተወሰኑት ብቻ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ተናግሯል፡፡

የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ እንዳሉት ባለሀብቶቹ ተሰማርተው የነበረው በሆልቲካልቸር የግብርና ስራ ላይ ነበር ብለዋል፡፡

ከስራ ከወጡት የተመለሱት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ከማለት ምን ያህሉ ወደ ስራ መመለሳቸውን በቁጥር አልተናገሩም፡፡

አሁን የግብርና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር እያዘጋጀው ያለው የ10 አመት የሆልቲካልቸር መመሪያ ባለሀብቱ በዘርፉ የተሻለ አምራችና በስፋት እንዲሰማራ የሚረዳ ነው ይላሉ፡፡

Comments

00:00