“ሕዝብን ሲያማርሩና ሲያንገላቱ ለነበሩ ተቋማት ሽልማት ሰጥቷል ከተባልኩኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ” የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት
TRACK

“ሕዝብን ሲያማርሩና ሲያንገላቱ ለነበሩ ተቋማት ሽልማት ሰጥቷል ከተባልኩኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ” የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት

00:00

ጥር 23 2017

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት “ሕዝብን ሲያማርሩና ሲያንገላቱ ለነበሩ ተቋማት ሽልማት ሰጥቷል ከተባልኩኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ” ሲል ተናገረ፡፡

ድርጅቱ ተቋማቱን ሲያወዳድር የውድድር ሒደቱ ከሙስናና ከብልሹ አሰራር የፀዳ ነውም ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በኩል ከዚህ ቀደም ሽልማት ያገኘ ድርጅት በምርቶች ላይ አላግባብ ዋጋ በመጨመሩ እንዲዘጋ መደረጉንም ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራት አሁን ላይ ሽልማት የሚገዙና የሚሸጡ በስፋት እየታየ መሆኑ አንስተው በእነኚ ሽልማት ሰጪ አካላት ምክንያት ሕዝብን የሚያንገላቱና የሚያማርሩ ተቋማት ሳይቀር ተሸላሚ እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ግን ለትርፍ የተቋቋመ ባለመሆኑ ከውድድር ሒደቱ ጀምሮ ያሉ ሒደቶች ከሙስና የፀዱ ናቸው፤ ሽልማት የሚያገኙ ተቋማትም በትክክል መስፈርቱን የሚያሟሉ መሆናቸውን እናረጋግጣለን ሲሉ ስራ አስፈፃሚው ነግረውናል፡፡

Comments

00:00