ሚያዝያ 9/2018
የበሬ ቆዳ በጥሬው ለምዕራብ አፍሪካ ለምግብነት እየተላከ መሆኑ፤ የቆዳ ፋብሪካዎችን እና ጥሬ እቃ አቅራቢዎቻቸውን እያወዛገበ ነው፡፡
ቆዳ አቅራቢዎቹ ያለምንም ልፋት በጥሬው ቆዳውን ለምግብነት ለሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት መላካቸው ፋብሪካዎቹን ጥሬ እቃ እያሳጣ ነው ተብሏል፡፡
መንግስት ቆዳ በጥሬው ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን ለመግታት በበሬ ቆዳ ላይ የ150 በመቶ የታክስ ጭማሪ ስራ ላይ አውያለሁ ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የበሬ ቆዳ ለምግብነት አገልግሎት ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የመላክ አዝማሚያ መጨመሩን የኢትዮጵያ የቆዳ አምራቾች ማህበር ተናግሮ ነበር፡፡
ምርቱ በዋናነት የሚላከው ወደ ቶጎ እና ናይጄሪያ እንደሆነም ማህበሩ አመልክቷል፡፡
ይህን ተከትሎ የቆዳ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ምርታቸውን ለቆዳ ፋብሪካዎች ከማቅረብ ይልቅ፣ ለምግብነት ወደ ውጭ መላክን የበለጠ አትራፊ ስላደረጉት፣ በአገር ውስጥ በሚገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች የጥሬ ዕቃ እጥረት አስከትሏልም ብሏል፡፡
Comments