00:00
ነሐሴ 16፣2016
ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን በመከላከል በሐምሌ ወር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሥነ ሕዝብ ድርጅት እውቅና ማግኘቷ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ያገኘችው ይሄው እውቅናም ከአፍሪካ ሀገሮች የመጀመሪያ እና ብቸኛ ያደርጋታል ተብሏል፡፡
ትናንት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቀንስ የበኩላቸውን ከውነዋል የተባሉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅውና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ በሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻ ላይ ምን ስለሰራች ነው ይህንን እውቅና ያገኘችው?
ለኢትዮጵያ የተሰጣት እውቅና በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ቀንሳለች በሚል ሳይሆን ያለ እድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን የማስቀረት ባደረገቸው ጠናካራ ስራ ነው ሲሉ የብሔራዊ ጥምረት የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አበባው ቦጋለ ነግረውናል፡፡
በ2025 ዓ.ም ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን ላመስቆም እሰራለሁ ብላ ቃል የጋባችው እንደ እ.ኤ.አ በ2015 ነበር፡፡
ነገር ግን ያንን ማድረግ ስላልቻለች ለቀጣዮቹ ስድስት አመታት ለማራዘም ውጥን መያዟን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡
መንግስት፣ የሀይማኖት ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታቸው በሀላፊነት ስራዎችን የሚከውኑ ከሆነ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን ይጠፋል ብለን እናምናለን የሚሉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ከዚህ ቀደም ስራዎችን ስንሰራ በነበሩበት አመታት እንደ ኮቪድ ያሉ ችግሮች እንቅፋት ሆነውብናል ብለዋል፡፡
Comments
00:00