00:00
ነሐሴ 2፣2016
ጎህ ቤቶች ባንክ በኢትዮዽያ አንድና ብቸኛ የሞርጌጅ ባንክ ነው።
ጎህ ቤቶች ባንክ አሁንም ዛሬም ያለውን ከፍተኛ የቤት ችግር ለመፍታት በተለያዩ መንገዶች እየተጓዘ ነው።
ቤት አቅራቢው፣ ፈላጊውና ገዢው በማይመጣጠንበት ገበያ ውስጥ ባንኩ ብዙ ፈተናዎችን አልፋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ በሐገር ውስጥ ከመሬት አቅርቦት ከፋይናንስ እጥረት ከኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ሌላም ችግር የሚያላቅቀውን አጋር ማግኘቱ ተሰምቷል።
ባንኩ ግሎባል ትሬድና ፋይናንስ ከተሰኘ አለምአቀፍ ኩባንያ ጋር በህብረት ለመስራት ውል ቋጥሯል።
አማካሪ ድርጅቱ ለጎህ ቤቶች ባንክ በሞረጌጅና ሪል ስቴት ዙሪያ የአለም አቀፍ ልምድና ጠባይ በማካፈል፣ የቬንቸር ካፒታል በማምጣት፣ የፋይናንስ አቅርቦት በማመቻቸት፣ በትብብር እንደሚሰራ የባንኩ ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ዲበኩሉ ለሸገር ነግረዋል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments
00:00