በኮሜሳ የዳኞች ሹመት ዙሪያ የቀረበው ክርክር ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በስራቸው ላይ ለመቆየት በሙሉ ድምፅ መስማማታቸው ተሰማ
TRACK

በኮሜሳ የዳኞች ሹመት ዙሪያ የቀረበው ክርክር ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በስራቸው ላይ ለመቆየት በሙሉ ድምፅ መስማማታቸው ተሰማ

Avatar

ሰኔ 6 2017

በኮሜሳ የዳኞች ሹመት ዙሪያ በኢትዮጵያዊው ጠበቃ በቀረበ ክስ ምክንያት የስራ ጊዜያቸው ያበቃ ዳኞች፤ የቀረበው ክርክር ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በስራቸው ላይ ለመቆየት በሙሉ ድምፅ መስማማታቸው ተሰማ።

የኮሜሳ ፍርድ ቤት በምስራቃዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ ባሉ አባል ሀገራት ውስጥ የንግድ ስምምነቶችን እና ታሪፍን ጨምሮ የሚነሱ ውዝግቦች የሚዳኙበት እና ኮሜሳ ካሉት አስራ አንድ ተቋማት መሀከል አንዱ ነው።

የኮሜሳ ፍርድ ቤትን የዳኞች ምልመላ ሂደትን በመቃውም ክስ የመሰረቱት ኢትዮጵያዊው ጠበቃ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የፓን አፍሪካ የጠበቆች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው።

Comments

Avatar