00:00
ታህሳስ 23፣2017
የምስራቅ ወለጋ ዞን ‘’ባለው ግጭት 128 የጤና ተቋማት ሙሉ ብሙሉ እና በከፊል ወድመውብኛል’’ አለ፡፡
በዚህም የተነሳ በየዛፍ ጥላ እና በኪራይ ቤቶች ጭምር የጤና አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ሲል ተናግሯል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከነበሩ የጤና ተቋማት 30 በመቶ ገደማዎቹ ተጎድተዋል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተብሏል፡፡
በከፊል አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትም በተሰባበረ እና ደረጃቸውን ባልጠበቀ መልኩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ይህንን ለሸገር ራዲዮ የነገሩት የምስራቅ ወለጋ ዞን የጤና መምሪያ ሀላፊ ቡልቶሳ ቡሻ ናቸው፡፡
በግጭቱ ወድመውና ተጎድተው ከነበሩት መካከል ዳግም በማህበረሰቡ የተገነቡ እንዳሉም ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ ዳግም የተገነቡትም የህክምና መሳሪያ ስለሌላቸው የሚሰጡት አገልግሎት ከደረጃ በታች ነው ብለውናል፡፡
በዞኑ የወደሙና የተጎዱ የጤና ተቋማትን መለሶ በማቋቋሙ የቻለ ሁሉ እንዲረዳን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
በዞኑ የጤና ተቋማት በተጨማሪ የምግብ እጥረት ስለሚያጋጥምም በዚሁ ዙሪያ ለሚሰሩ ድርጅቶች እርዳታ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንም እንኳ በዞኑ ብዙ የጤና ተቋማት የወደሙ ቢሆንም ወረርሽኞች እንዳይስፋፉ ባለሞያዎች ቤት ለቤት እየሄዱም የጤና አግልግሎት ስራ እየሰሩ ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፍቅሩ አምባቸው
Comments
00:00