ሚያዝያ 15/2018
በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን እና አጣዳፊ የምግብ እጥረት ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
ይህንን ፕሮጀክት ይፋ ያደረገው ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ሲሆን ፕሮጀክቱ ለስድስት ወር እንደሚቆይ እና 4.5 ሚሊዮን ዶላር እንደተመደበለትም ሰምተናል።
የድርጅቱ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር አንበሱ ቶላ (ዶ/ር) እንዳሉት ይህ ባለብዙ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጀክት በጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ እና በንፁህ መጠጥ ውሃ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ ነግረውናል።
የ4.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት ፕሮጀክቱ ለዚህም በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ (EHF) ድጋፍ አድርጓል።
Comments