የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው ረቂቅ ሰነድ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት ሚዛናዊ ያልሆኑ ጉዳዮች የተካተቱበት ነው ተባለ
TRACK

የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው ረቂቅ ሰነድ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት ሚዛናዊ ያልሆኑ ጉዳዮች የተካተቱበት ነው ተባለ

Avatar

ግንቦት 19፣2016

የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ያወጣው ረቂቅ አለም አቀፍ የወረርሽኝ ስምምነት ሰነድ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት ሚዛናዊ ያልሆኑ ጉዳዮች የተካተቱበት ነው ተባለ።

አለምአቀፍ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ በተለይ ቀዳሚ ተጎጂ የሚሆኑት ታዳጊ ሀገራት በመሆናቸው ሰነዱ ቢጸድቅ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው ተብሏል።

ኤድስ ሔልዝኬር ፋውንዴሽን ኢትዮጵያ እና የሲቪል ማህበራት አጋሮቹ በወቅታዊው የዓለም ጤና ድርጅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ የስምምነት ሰነድ ላይ ያተኮረ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ በሰጡበት ጊዜ ነው እንዲህ የተባለው።

በመግለጫውም የአለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የወረርሽኝ የስምምነት ሰነድን እንዲያሻሽል ፣ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆንም ተጠይቋል።

ምህረት ስዩም

Comments

Avatar