TRACK
የሌሎችን ጥበባዊ የፈጠራ ውጤት ያለፈቃድ መጠቀምና የባለቤትነት መብትን ተጋፍቶ ማሰራጨት ለፈጠራ ባለቤቶች አሁንም ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡
ጥር 27/2018
የሌሎችን ጥበባዊ የፈጠራ ዉጤት ያለፈቃድ መጠቀምና የባለቤትነት መብትን ተጋፍቶ ማሰራጨት ለፈጠራ ባለቤቶች አሁንም ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የፈጠራ ባለቤቶችን የስራ ዉጤት መመንተፍ ዘርፉም አይነቱም ብዙ እንደሆነ የሚያነሱት በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ወሰን ሙሉ እንደውም የፈጠራ ስራዎችን ያለፈቃድ መጠቀም እንደ ዘመናዊና ስልጣኔ ተቆጥሮ ቴክኖሎጂው በረቀቀ ቁጥር የሙዚቃ፣ የፊልም እና የጽሁፍስራዎች ያለአንዳች ከልካይ ሲባዙና ሲሰራጩ እንደሚስተዋሉ አንስተዋል ።
አብዛኛዉን መንታፊዎቹ ራሳቸዉን መደበቃቸዉ፣ የፈጠራ ባለቤቶች ተከታትሎ ያለመጠየቅ ፣የቴክኖሎጅዉም በፍጥነት መለዋወጡ እና ሌላዉም ሌላዉም ተደማምሮ ችግሩን እንዳባባሰዉ ሀላፊዉ አብራርተዋል፣፣
Comments