በሰሜ ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ 110,563 ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ
TRACK

በሰሜ ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ 110,563 ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ

Avatar

ታህሳስ 16፣2017

በሰሜ ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ 110,563 ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ፡፡

ለእነዚህ ተጎጂዎች ለመድረስ ለአንድ ዙር ብቻ 16,600 ኩንታል የምግብ ድጋፍ እንደሚስፈልግ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ነግሮናል፡፡

ከዚህም ውስጥ በፌዴራሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በኩል 4,000 ኩንታል ያህሉ ወደ አካባቢው እየገባ መሆኑንና ለተጎጂዎች ማሰራጨት መጀመራቸውን የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አለሙ ይመር ነግረውናል፡፡

በሌላ በኩል ወደ አካባቢው እየተጓጓዘ ነው ከተባለው የምግብ እህል ቀደም ብሎ መድሃኒትና አልሚ ምግቦች የሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ህፃናት ባሉባቸው ሁለት ወረዳዎች መሰረጨታቸውንም ሃላፊው ጨምረው ነግረውናል፡፡

በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ሰሜን ወሎ አካባቢ መውጣትም ይሁን መግባት ባለመቻሉ፤ለሁለት ወራት ያህል የእለት ደራሽ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ተከስቷል ብለዋል ሃላፊው፡፡

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar