00:00
የካቲት 26 2017
ተማሪዎች በሂሳብ እና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ላይ ያሉባቸውን ክፍተቶች ይሞላል የተባለ ማጠናከሪያ ትምህርት በቴሌቪዥን አስጀመርኩ ሲል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናገረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተማሪዎች የቴሌቪዥን ማጠናከሪያ ትምህርት ከትናንት ከየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መከታተል ትችላላችሁ ብሏችኋል፡፡
በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ትብብር ይቀርባል የተባለው የቴሌቪዥን ማጠናከሪያ ትምህርት በተመረጡ መምህራን ተዘጋጅቷል ተብሏል።
በትምህርት ዘርፉ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እየሰራሁ ነው ያለው አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮው በተለይ ደግሞ በሂሳብ እና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ላይ ክፍተት መኖሩን አይቻለሁ ብሏል፡፡
ይህንንም በሂሳብ እና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ላይ የሚታይን ውስንነት ለመቀነስ የቴሌቪዥን ማጠናከሪያ ትምህርት አሰናድቻለሁ ብሏል።
Comments
00:00