በባህር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የኢንተርኔት ኬብል ወይም ገመድ እንዳይቋረጥ ዘላቂ የሆነ አሰራር ሊያበጅ ይገባል ተባለ
TRACK

በባህር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የኢንተርኔት ኬብል ወይም ገመድ እንዳይቋረጥ ዘላቂ የሆነ አሰራር ሊያበጅ ይገባል ተባለ

00:00

መንግስት በጎረቤት ሀገራት በኩል በባህር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የኢንተርኔት ኬብል ወይም ገመድ እንዳይቋረጥ ዘላቂ የሆነ አሰራር ሊያበጅ ይገባል ተባለ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በበኩሉ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በ5 አቅጣጫዎች የኢንተርኔት ገመድ ወደ ሃገሯ ስላስገባች የመቋረጥ ስጋት የለም ብሏል፡፡

የኢንተርኔት ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ቻምበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት ሙላቱ ኢትዮጵያ የሯሷ የባህር በር ስለሌላት የኢንተርኔት ኬብል ወይም ገመድ በባህር በኩል ወደ ሀገሯ ለማስገባት የሌሎችን ሃገራት ትብብር ትሻለች ብለዋል፡፡

ባህር ውስጥ የኢንተርኔት ገመድ ቢቆረጥ ሃገሪቱ አገልግሎቱን ማስቀጠል አትችልም ያሉት ዶክተር አስራት ይህንን ስጋት ለማስቀረት ከወዲሁ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በጋራ ልንሰራበት ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድኤታ ዶክተር ይሽሩን አለማየሁ ኢትዮጵያ አሁን በጅቡቲ ፣ሱዳን እና ኬንያ ጨምሮ በ5 በኩል ነው የኢንተርኔት መስመሮችን ወደ ሃገር ውስጥ እያስገባች በመሆኑ አማራጭ በመኖሩ ይቋረጣል የሚል ስጋት እንደ መንግስት የለም ብለዋል፡፡

Comments

00:00