የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት ታሪካዊው ስፍራ እድሳት ተደርጎለት ለህዝብ ክፍት ሊሆን ነው
TRACK

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት ታሪካዊው ስፍራ እድሳት ተደርጎለት ለህዝብ ክፍት ሊሆን ነው

Avatar

መስከረም 10፣2017

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት ታሪካዊው ስፍራ እድሳት ተደርጎለት ለህዝብ ክፍት ሊሆን ነው፡፡

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ጆሞ ኬንያታ፣ ከጋናው ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ንኩሩማህ፣ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋማል አብዱል ናስር፣ ከታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ፣ ከጊኒው ሴኮ ቱሬ እና ከሌሎችም መሪዎች ጋር በመሆን ነበር የቀድሞውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት ግንቦት 20 ቀን 1955 ዓ.ም የመሰረቱት፡፡

የዛሬ 61 ዓመት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረት እነዚህ የህብረቱ መስራቾች ፊርማቸውን ያኖሩት በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ECA) ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለውና ''African Hall'' በመባል በሚታወቀው ህንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር፡፡

ቦታው የህብረቱ መመስረቻ በመሆኑ ታሪካዊ ከመሆኑም ባሻገር ሌሎች ቅርሶችንም የያዘ ነው።

ቅርሶቹ በእርጅና ብዛት ከጥቅም ውጭ ከመሆናቸው በፊት እድሳት ያስፈልጋቸዋል ተብሎ በመታመኑ የቅርሱ ባለቤት የሆነው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ላለፉት 2 ዓመታት እድሳት ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡

Comments

Avatar