‘’ባለፉት  47 ዓመታት ሳስተዳድራቸው የነበሩ  ቦታዎችን በድንገት ልቀቅ ተባልኩኝ’’ እንረዳዳ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር
TRACK

‘’ባለፉት 47 ዓመታት ሳስተዳድራቸው የነበሩ ቦታዎችን በድንገት ልቀቅ ተባልኩኝ’’ እንረዳዳ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር

Avatar

ሐምሌ 9፣ 2016

‘’ባለፉት 47 ዓመታት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አትላስ እና ደሳለኝ ሆቴል አካካቢዎች ሳስተዳድራቸው የነበሩ ሁለት ቦታዎችን በድንገት ልቀቅ ተባልኩኝ’’ ሲል እንረዳዳ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ፡፡

ማህበሩ ቦታዎቹን ከመንግስት የተረከበው በ1969 ዓ.ም መሆኑን ተናግሮ፤ የሁለቱ ቦታዎች ስፋትም በድምሩ 8,100 ካሬ ሜትር መሆኑን አስረድቷል።

እንረዳዳ ሲመሰረት "የመኖሪያ ቤቶች ሕብረት ስራ ማህበር" ሆኖ እንደነበር የሚያስታውሱት የማህበሩ አባላት በዚህም ማህበሩ ለ147 ሰዎች ቤት መስራቱን ይጠቅሳሉ፡፡

ከቤት ግንባታው የተረፈው 8,100 ካሬ ሜትር ቦታውን እንረዳዳ የሕብረት ስራ ማህበርን በማቋቋም የተለያየ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱ ተነግሯል።

Comments

Avatar