TRACK
በአዲስ አበባ በልማት ተነሺ የሆኑና ሰነድ ማግኘት ሲገባቸው በወቅቱ ሰነድ ያላገኙ ቤቶች ምትክ ቦታ እንደሚሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተናገረ
ህዳር 6፣ 2017
በአዲስ አበባ በልማት ተነሺ የሆኑና ሰነድ ማግኘት ሲገባቸው በወቅቱ ሰነድ ያላገኙ ቤቶች ምትክ ቦታ እንደሚሰጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተናገረ።
ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም በልማት የተነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ያነሱት የነበረው የመሰረተ ልማት አለመሟላት ቅሬታ አሁን ላይ ችግሮቹ እየተፈቱ ነው ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በህጋዊ መንገድ የተገነባ ነገር ግን በወቅቱ ሰነድ ማግኘት ሲገባቸው ሰነድ ያላገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በልማት ለፈረሰባቸው ምትክ እንደሚያገኙ ተናግረዋል ።
በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት የተነሱ የማህበረሰብ ክፍሎች በምትኩ ያገኙት ቤት እና አከባቢ የመሰረተ ልማት ችግር እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጃንጥራር አሁን ላይ እነኚህ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ተፈተዋል ባይባልም በተወሰነ መልኩ ችግሮቹን እየፈታን ነው ብለዋል።
Comments