TRACK
ፍርድ ቤቱ በእነ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለፊታችን ጥር 29 ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ
00:00
ጥር 21 2017
ፍርድ ቤቱ በእነዮሃንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለፊታችን ጥር 29 ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
አቶ ዮሃንስ ቧያለውና አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 51 ግለሰቦችን ባካተተው የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 16ቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
በትላንትናው እለት ስለዋለው ችሎት የጠየቅናቸው ከተከሳሾች ጠበቆች መካከል የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ተከሳሾቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርበዋል ብለዋል።
ጠበቃው ስለ ችሎቱ ሲያስረዱ ችሎቱ ከዚህ ቀደም ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሸሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፣ ዐቃቤ ሕግም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በመጠየቁ ጉዳዩ ለአራት ወራት ሳይንቀሳቀስ ቆይቷል፤
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የከፍተኛውን ወይም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናቱ እና ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በማዘዙ በትላንቱ ችሎት እገዳው ተነስቶ መዝገቡ ተንቀሳቅሷል ብለውናል፡፡
Comments
00:00