00:00
መስከረም 2፣2017
ከበዓሉ ዋዜማ እስከ ዛሬ መስከረም 2 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የ2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል እንዴት አለፈ ስንል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቀናል፡፡
የ��ሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡን ምላሽ ከዋዜማው ጀምሮ በተከሰቱት የትራፊክ አደጋዎች የ4 ሴቶችና የ2 ወንዶች ሰዎች ይህወት አልፏል ብለዋል፡፡
በዚህም በበዓሉ ዋዜማ ጳጉሜ 5 ቀን በጉለሌ ክፍለ ወረዳ 6 ቀለበት መንገድ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ የ35 ዓመት ግለሰብ ህይወቱ አልፏል፡፡
Comments
00:00