''የአውሮፕላን ማረፊያው፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃል''
TRACK

''የአውሮፕላን ማረፊያው፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃል''

Avatar

ታህሣስ 2፣2017

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ ይሆናል የተባለ፤ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የቦታ ርክክብ ተደረገ፡፡

መለስተኛ አውሮፕላኖችን እንዲያስተናግድ ታሳቢ ተደርጎ ይገነባል የተባለው ይህ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃልም ተብሏል፡፡

የአውሮፕላን ማረፊያው የሚገነባው በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ መሆኑ ተነግሯል፡

ግንባታው የሚከወነው በአቢሲኒያ ፍላይት እና በቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር አማካኝነት እንደሆነ ሰምተናል፡፡

አሁን ርክክብ የተደረገው ቦታ ስፋት 6 ሄክታር መሆኑንና እንደየአስፈላጊነቱ ሊሰፋም ይችላል ተብሏል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ

Comments

Avatar