የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የነበረው የጸጥታ ችግር ተፈትቶ አሁን ሰላም ስለሰፈነ የወደሙ የጤና ተቋማትን በማቋቋሙ እርዱኝ ብሏል
TRACK

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የነበረው የጸጥታ ችግር ተፈትቶ አሁን ሰላም ስለሰፈነ የወደሙ የጤና ተቋማትን በማቋቋሙ እርዱኝ ብሏል

00:00

ታህሳስ 23፣2017

በነበረው ግጭት ምክንያት 128 የጤና ተቋማት ሙሉ ብሙሉ እና በከፊል ወድመውብኛል ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡

በክልሉ አሁን ሰላም ስለሰፈነ የወደሙ የጤና ተቋማትን በማቋቋሙ እርዱኝ ብሏል፡፡

መተለከል እና ካማሺ ዞኖች ደግሞ በግጭቱ ይበልጥ የጤና ተቋማት የወደሙባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ይህንን የነገሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ ናቸው፡፡

የደረሰው ጉዳት ተጠንቶ ለፌዴራል መንግስት ሪፖርት ተድርጓልም ብለውናል ሀላፊው፡፡

ነገር ግን በጤና ተቋማቱ የደረሰው ውድመት በመንግስት አቅም ብቻ መልሶ ለመገንባት የሚከብድ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments

00:00