ሚያዝያ 17 2017
ወደ ወንዝ የሽንት ቤት ፍሳሽ ለቃችኋል፣ በህገ ወጥ ንግድ፣ ግንባታ በመሳሰሉት ተሳትፋችኋል ከተባሉ ሰዎችና ተቋማት ባለፈው ዘጠኝ ወር 275 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡
ደንብ አስከባሪ መስሪያ ቤቱ ‘’ግንዛቤ ሳይሰጥ ቅጣት ላይ በርትቷል’’ በሚል ቢተችም ‘’እኔ ግን አልቀበለውም’’ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን ባልሰራ ተቋማትና ግለሰቦች የሚከፍሉት የቅጣት መጠን ከአሁኑ በእጥፍ ይሆን ነበር ብሏል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከወንዝ ዳር ልማትና ከፈሳሽ አወጋገድ ጋር ተያይዞ የጥፋቱ የቅጣት መጠን ወስኖ መቅጣት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ግንዛቤ ሳይኖረንና አስቀድሞ ሳይነገረን ወደ ቅጣት መገባቱ ተገቢ አይደለም በማለት ይናገራሉ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበኩሉ አሁን ላይ ገቢው ከፍ ያለ ቢመስልም የደንብ ጥሰቶቹን ባልከላከል ከዚህ ይበልጥ ነበር ሲል መልሷል፡፡
Comments